Skip to content
Advertisements

Category: ጨዋታ

ካለ ሰው…

ከነድህነቱ ወዘናው ፊቱ ላይ ጨፍ ያለ ምስኪን፤ ዘሩ ምን ሆነ ምን፥ ፈገግታው ከልቡ ፈልቆ ፊቱ ላይ፣ ጥርሱ ላይ፣ ዐይኑ ላይ፣ ግንባሩ ላይ ሁሉ የሚከለበስ ድሃ። ቂጡ ሁላ የሚስቅለት ዕድለኛ፥ ምንም የሌለው፣ ሁሉም ያለው። የአዲስ አባ ሰው፣ የአገር ሰው!   ገመድ እና አንድ ሁለት የተሳሉ ማረጃ ቢላዋዎችን ይዞ አሳራጅ የሚቃርም በሬ አራጅ። የበግ ቆዳ ያሌው። በአዲስ ልብስ ያሸበረቁ፣ በአዲስ ልብስ እና በጸዴ ምግብ ተስፋ በቀብድ የሚቦርቁ ሕጻናት።   እዚህ እና እዚያ በወዳደቀ ቀጤማ፣ መንገዱም የበዓል ይመስላል። የሚነሳለት ቆሻሻ ባይኖርም፣ ሁሉም የበዓል መልኩን ይይዛል። በፍቅር ዐይን እንደሚያዩት ሁሉ፣ ያምራል! በዋዜማ እና በእለቱ… Read more ካለ ሰው…

Rate this:

ችግር ወልዶ ያሳደገውን ፍቅር፣ ማግኘት ይቀብረዋል!

ችግር ወልዶ ያሳደገውን ፍቅር፣ ማግኘት ይቀብረዋል! በአንድ ትሪ ማቅረብ ያመጣው ችግር ቢሆንም (ሲመስለኝ)፥ ለልጆች መተሳሰብን፣ አንተ ብስ አንቺ መባባልን አስተምሯል። ሁሉም ሰው ታጥቦ እስኪሰየም ድረስ እንጠባበቃለን። ከአንዱ ቦታ እንጀራው ሲሳሳ፣… Read more ችግር ወልዶ ያሳደገውን ፍቅር፣ ማግኘት ይቀብረዋል!

Rate this:

ከማዕበሉ ባሻገር…

እንደሚታየው፥ ሁላችንም በፍስሀ እና በእርካታ፣ በስሜት ማዕበሉ ላይ ጡዝ ፍንጥዝ እያልን ያለበት ሁኔታ ነው ያለው። ይኽን ያሳየን አምላክ ክብር ምስጋና ይግባው!   ሚዲያዎቹም፣ አክቲቪስቶቹም፣ ፖለቲከኞቹም፣ ጋዜጠኞቹም… ሁሉም በአንድ ዓይነት አጀንዳ ተወስዶ፣ በአንድ ዓይነት ግብር ተጠምዶ …ደፈር ብሎ የህግ የበላይነት ይከበር የሚል እና ስለፍትህ የሚጮኽ፤ ስሜታችንን ደርዝ በማስያዝ፥ ለነገ የጋራ ጉዳዮች እንድንዘጋጅ አቅጣጫ የሚጠቁም፤ የንግግር ባህላችን እንዲሻሻል የተለያዩ ዝግጅቶችን የሚያቀርብ፤   ቢያንስ ፍቅርን እና አንድነትን በሚያደረጅ መልኩ፥ ድሮ እነ ሂሩት መንግስቴ በ”ከሴቶች አድማስ” በ”ከያቅጣጫው” ዓይነት ፕሮግራሞች ዙሪያ ገባውን ያስቃኙን እንደነበረው፣ የገጠር እና የከተማ ማሕበረ – ባህላዊውን መስተጋብር፣ እና የጋራ እሴቶቻችንን ዓይነት… Read more ከማዕበሉ ባሻገር…

Rate this:

ከዚያስ…?

“እሺ፥ እንዴት ነው? ሁሉ ሰላም?” አልኩት አፍሪካ አሜሪካዊውን አዲስ ወዳጅ “ማለት?” እኔ ከዝምታዬ ጋር ስደራደር፣ በሀሳብ ጭልጥ ብሎ ስለነበር ተደናግጦ ጠየቀኝ “አይ፣ እንዲያው ሁሉ ሰላም ነው ወይ? ቤተሰብ? ኑሮ እንዴት እየወዘወዘህ ነው? ለማለት ያህል ነው።” ቀልጠፍ ብዬ በፈገግታ ታጅቤ መለስኩ። የምሸሸው ጭንቀት ስለነበረብኝ ዝምታውን አልፈለግኩትም። “ኦህ፥ ሁሉም ሰላም። ሰላም ነው። …እሁድ የትልቁ ልጄ 29ኛ ዓመት ልደት ነበር።” “እየቀለድክ መሆን አለበት። 29? አንተ ራስህ ከዚያ የምታልፍ አትመስልም እኮ።” “አዎ። ሁለተኛዋ 26 ዓመቷ ነው።” “በጣም ደስ ይላል። እጅግ በጣም ደስ የሚል ነገር ነው። ይኽኔ ከኮሌጅም ወጥተው ቦታ ቦታ ይዘውልሃላ…” “አይ አይ! ቢሆን… Read more ከዚያስ…?

Rate this:

ስለመውደቅ…

ሰፈሬ ልጅ ገና ሊወድቅ ሲያስብ፥   “አንተ ልጅ ዋ… ቀስ ብለህ ተጫወት…” “ዋ ብያለሁ…” “እሺ ኋላ እሪ ብትል ምናለች እንዳትል…” “ትደፋና ኋላ…ዋ” (“ውይ ተዪው አንቺ ደግሞ። ይጫወቱ እስኪ። ሸክላ ነው ልጅ ሁሉ ሲጫወት ተለይቶ ምን እንዳይሆን ነው? እሺ ከዚያስ…” የሚል ወሬ የተጠማ ድምጽ ፊቸሪን ሊገባም ይችላል።) ብዙ የማስጠንቀቂያ መዓት ይጎርፍበታል።   ልጁ ልጅ ከሆነና፥ አስጠንቃቂዋ እናቲቱ ከሆነች በዐይኗ እየተከታተለቸው ሲወላገድ ትወላገዳለች፣ ሲወድቅ ትወድቃለች። አይሞቀውም እንጂ፣ አያውቀውም እንጂ፣ አንቀልባ አልጣለችበትም እንጂ፣ እየሄደ መስሎታል እንጂ፥ በዐይኗ አቅፋው ነው የሚራመደው።   ከዚያ ተፍ ተፍ ብሎ ባፍጢሙ ይደፋላቸውና፥ አቀባብሎ እንደሚጠብቅ ሁሉ ሰፈሩ ባንድ እግሩ… Read more ስለመውደቅ…

Rate this:

“ሄዋን እንደዋዛ”

“ሄዋን እንደዋዛ ፍሬዋን በልተሽ በእኔና በምድር፣ ሞት እንዳመጣሽ”   የሚላት የመጀመሪያዋን ቀዳማዊት ሄዋን ነው   “ለባከነው ልቤ ራርቶ ልብሽ መጽናናያ ሆኖኛል፣ ክሶኛል ፍቅርሽ”   ሲል ደግሞ ይኽቺ ዳግማዊት ሄዋን እመቤታችን ማርያም ሆና፣ በልጇ በክርስቶስ እንደካሰችን ነው የሚያሳየው።   ~ ቴዲ አፍሮ ❤   “ልቤም ተደላደለ ጎኔም ደላው መሰለኝ አንቺን ስለመውደዴ፣ አገር ሰምቶ ጉድ ቢለኝ ከወደድኩሽ ወዲያ ምንድን ነው? ቢጠፋም ስሜ ነው። በዚህች ዓለም ስኖር ሰው ነበር ረሀቤ ምኞቴ ተሳካ ባንቺ አረፈ ልቤ…”   እያለ ነው እንግዲህ ዘፈኑ ጀምሮ……….   “ሄዋን እንደዋዛ ፍሬዋን በልተሽ በእኔና በምድር፣ ሞት እንዳመጣሽ ለባከነው ልቤ ራርቶ… Read more “ሄዋን እንደዋዛ”

Rate this: