Skip to content
Advertisements

Category: ግጥም

ሴት ነሽና

ሴት ነሽና፥ ሰውነቱን፣ ክብሩን ትቶ፣ ቀሚስሽን ወንድ ይለካል ደግሞ ሲለው ተንጠራርቶ ተጠራርቶ… ደፍሮ ይነካል፤   ሴት ነሽና፥ “ተው” ብትዪው፥ እንደመብቱ “ዝም በይ” ይላል በአንደበቱ፤ ማንም የለም “ተው” የሚለው፣ ሁሉም አጋዥ አበርቺው ነው፤   ሴት ነሽና፥ የሀሳብሽን ቁመት ልቀት የህልምሽን ስፋት ርቀት ወንድ ሰፍሮ ይመዝናል፣ በእርሱ ገበያ ይተምናል፤   ሴት ነሽና፥ በአውሬነቱ እርቃን ቀርቶ፣ ሀፍረት ጥሎ፣ ሱሪ ፈትቶ፣ ሰው ገላ ላይ ይፈነጫል፣ “አሳስታኝ ነው” ብሎ ይጮሃል፤   ሴት ነሽና፥ ለእርሱ ስሜት ለአውሬነቱ ጥጋት ሆኖ ለነውሩ፣ ለሴሰኛ ሟችነቱ አንቺን ያማል ሁሉም ወጥቶ ከየቤቱ፤   ሴት ነሽና፥ እሱ ሰፍሮ አጥሯል ብሎ የደፈረሽን ተንጠላጥሎ፣… Read more ሴት ነሽና

Rate this:

እንደወረደ! ;)

የቤቲን እና የዶ/ር ደሳለኝን ቃለ መጠይቁን አየሁት። የተባለውን ያህል የተጋነነ ሆኖ ግን አላገኘሁትም። ደሳለኝ አለመዘጋጀቱ ያስታውቃል። መዘጋጀት ሲባል፣ ለቃለ መጠይቅ ሳይሆን፣ በአጠቃላይ እንደ ፓርቲ አመራር ራሱን በብዙ ነገሮች ውስጥ ማለማመድ እና ነጥሮ የወጣ ሀሳብ/መልስ የሚሆን ነገር ማዘጋጀት ነበረበት። አባላቱም እንዲሁ ማድረግ ነበረባቸው። ለከእንግዲውም መዘጋጀት አለባቸው።   በዋናነት ደሳለኝን የማይሆን ነገር ውስጥ የከተተው ጋሻው እና ክርስቲያን የተባሉ ስራ አስፈጻሚ አባላቶቹ ያደረጉትን ያልተገባ እና ያልበሰለ ንግግር ለማስተባበል እና “ማለት የፈለጉት” እያለ፣ ያላሉትን ሊልላቸው እና ያሉትን ሊያለባብስላቸው ባደረገው ጥረት ነው።   ከዚህ የምንማረው/የምንረዳው፣ አባላቱ (እንዲሁም ሌሎቻችን) ከፌስቡክ ወጣ እያሉ ወደ መጽሐፍት ገጾች አየት… Read more እንደወረደ! 😉

Rate this:

የአገሬ መልክ ነው

የለበስሽው ቀሚስ እገላሽ ላይ ነትቦ፣ የለበስሽው ሸማ፥ ልጅ ኑሮ ያሳደፉት፥ ከላይሽ ተስቦ ወልደሽ ባሳደግሽው፣ ደም ጡት በቀለብሽው ከመሶብ እንጀራ ባላጎደልሽበት፣ ጉያሽ በሸሸግሽው፣ በአብራክ ክፋይ እብሪት፣ ፊት ጀርባሽ ተነክሶ ተስቦ ከመሬት… Read more የአገሬ መልክ ነው

Rate this:

“Donkey Meat Up for Export, Slaughterhouse Opens” – Fortune

ሲለፋ የኖረው በሸክም በዱላ የአህዮቹ ገላ ቀረበ ተልኮ፣ በጀማው ሊበላ ታጨ ለስል ቢላ። * * * ተርፏቸው ሳይሰጧት “ማር አይጥማት” ሲሉ በስሟ ቀን ግፊያ “አለች አሉ አህያ” ብለው ሲደልሏት ሲያነሱ… Read more “Donkey Meat Up for Export, Slaughterhouse Opens” – Fortune

Rate this:

ስለ ውሃ

“ኧረ ውሃ ውሃ…” እያለ ውሃን በማሰብ የኖረ፣ አፉ የደረቀበት እና ቧንቧው የዛገበት ሰው፥ የዓለም የውሃ ቀንን በምን አስቦት ይውላል? – በግጥም? ቀናቱ የተጎራበቱትስ ለደሀው ሰቀቀን ማስታመሚያ አማልክቱ ፈርደው ይኾን?  … Read more ስለ ውሃ

Rate this: