Skip to content
Advertisements

Category: ከእለታት በአንዱ ቀን…

ከአዋላጅ ነርስ ወዳጄ ጋር ገጠመኝ

ጊዜ ሳገኝ ስለህክምና ባለሞያዎች የማስታውሰውን እጽፋለሁ ባልኩት መሰረት፥   ጎሮ የሚባል ጤና ጣቢያ ስር ያሉ የጤና ኬላዎች (health posts) የCHIS (community health information system) የሥራ ላይ ስልጠና ለመስጠት ከአንዲት አዋላጅ ነርስ የስራ ባልደረባዬ ጋር እንሄድ ነበር።   ነገሩ፥ የትራንስፖርት ችግርም ስለሚኖርብን በአንድ ድንጋይ ብዙ ወፍ ለመግደል ተሰብስበን ነበር የምንሄደው። እዚያ ደርሰን ሁላችንም በየሚናችን እንሰማራለን።   የዚያን ቀን ግን ጤና ኬላው አንዲት ነፍሰጡር እናት ምጥ ላይ ሆና፣ የጤና ኤክስቴንሽኖቹም ሊረዷት እየሞከሩ ግራ ተጋብተው ሲጯጯሁ ነበር የደረስነው። እርግዝናው ከመደበኛው ትንሽ የተወሳሰበ (complicated) ነገር ነበረው።   “ለምን አምቡላንስ አልጠራችሁም ቀድማችሁ?” ብላ ጮኸች ባልደረባዬ… Read more ከአዋላጅ ነርስ ወዳጄ ጋር ገጠመኝ

Rate this:

ከዚያስ…?

“እሺ፥ እንዴት ነው? ሁሉ ሰላም?” አልኩት አፍሪካ አሜሪካዊውን አዲስ ወዳጅ “ማለት?” እኔ ከዝምታዬ ጋር ስደራደር፣ በሀሳብ ጭልጥ ብሎ ስለነበር ተደናግጦ ጠየቀኝ “አይ፣ እንዲያው ሁሉ ሰላም ነው ወይ? ቤተሰብ? ኑሮ እንዴት እየወዘወዘህ ነው? ለማለት ያህል ነው።” ቀልጠፍ ብዬ በፈገግታ ታጅቤ መለስኩ። የምሸሸው ጭንቀት ስለነበረብኝ ዝምታውን አልፈለግኩትም። “ኦህ፥ ሁሉም ሰላም። ሰላም ነው። …እሁድ የትልቁ ልጄ 29ኛ ዓመት ልደት ነበር።” “እየቀለድክ መሆን አለበት። 29? አንተ ራስህ ከዚያ የምታልፍ አትመስልም እኮ።” “አዎ። ሁለተኛዋ 26 ዓመቷ ነው።” “በጣም ደስ ይላል። እጅግ በጣም ደስ የሚል ነገር ነው። ይኽኔ ከኮሌጅም ወጥተው ቦታ ቦታ ይዘውልሃላ…” “አይ አይ! ቢሆን… Read more ከዚያስ…?

Rate this:

‘የአስተማሪ ምግብ…’

ዩኒቨርስቲ አስተምር የነበረ ጊዜ…   ከእለታት ባንዱ ቀን ቡና ልጠጣ ወጥቼ ጠረጴዛ የተጋራኋቸው ሁለት ባልደረቦቼ ብስጭትጭት ብለው ሲያወሩ ሰማኋቸው።   “ምንድን ነው እሱ?” አልኩኝ ከመቀመጤ።   “እንዴት እንዴት እንደጠገቡ እኮ…” አለኝ አንዱ።   (በኋላ ግራ ቀኙን ስቃርም የገባኝ ሁሉም በየጠረጴዛው ያወራ የነበረው ይህንኑ ጉዳይ ነበር።)   “እነማን ናቸው ደግሞ?”   “ሌላ ማን ይሆናል? እነዚህ የተረገሙ ናቸዋ”ብሎ ተማሪዎች ወደሚራመዱበት አቅጣጫ አገጩን ቆለመመው።   “ተማሪዎቹ? …ምን ተባለ ደግሞ?” አልኩት እንዲህ መነጋገሪያ የሆነውን ጉዳይ ለመስማት አቆብቁቤ።   “እዚህ ላውንጅማ ድርሽ አይሏትም። እንደውም በዲሲፕሊን ኮሚቴ መከሰስ አለባቸው።” አለኝ።   “ጋይስ እኛም እኮ መምህራን ነን።… Read more ‘የአስተማሪ ምግብ…’

Rate this:

የወዳጅን ሞት ሰምቼ ስባዝን…

ማኅበራዊ መዋቅራችን አጓጉል ነው። ከደስታ ይልቅ ኀዘንን ለማስታመም ይቀለናል። ከእልልታ ይልቅ ለከንፈር መጠጣ የሚያፈጥነን ይመስላል። በሰው ደስታ ከምንደሰተው ይልቅ፣ ሰዎችን ለተሻለ ፍላጎታቸው ከምንገፋቸው ይልቅ፣ በኀዘናቸው የምንማቅቀው ይበዛል፤ ከፍላጎታቸው ምንገፈትራቸው ይልቃል።… Read more የወዳጅን ሞት ሰምቼ ስባዝን…

Rate this:

ወይ ጉድ…

ከዓመት ከምናምን በፊት…   “አብሬያቸው ብሰራ” ከምላቸው፣ ጥሩ ስሜት ካሉኝ መሥሪያ ቤቶች መካከል በአንዱ የሥራ ማስታወቂያ መውጣቱን ጋዜጣ ላይ ተመልክቼ ለማመልከት አሰብኩና የትምህርት እና የሥራ ማስረጃዎቼን አደራጅቼ ሄድኩ። (መቼም አብዛኛው ቅጥር በፖለቲካ አቋም፣ በትውውቅና በዝምድና እንደሆነ ባላጣውም፥ በምናልባት ነበር ሙከራው።)   ከወጡት ሶስት የሥራ መደቦች እኔ ለማመልከት የፈለግኩት “managing director” ይል የነበረውን የሥራ መደብ ነበር። (ቀሪዎቹ ሁለቱ Data Encoder እና Secretary ነበሩ።) መስፈርቱን በበቂ ሁኔታ ስለማሟላ “ለቃለ መጠይቅ ፈተና ቢጠሩኝ እንኳን…” የሚል ጉጉት ነበረኝ።   ቢሮው ደረስኩኝና የሰው ሀብት አስተዳደሯን (መሰለችኝ) “ጤና ይስጥልኝ፣ የሥራ ማስታወቂያ አይቼ ለማመልከት ነበር።” አልኳት።  … Read more ወይ ጉድ…

Rate this:

“ትናንት” እና “ዛሬ”

ብዙ ጊዜ፥ የትናንቱን የማድነቅና የዛሬን ሰው የማኮሰስ ነገር አለ። በተለይ ከወዲያኛው ትውልድ ያሉ ሰዎች ያዘወትሩታል። ከወዲህም፥ “ዛሬ ቅቤ ንጠን ትናንትን እንቀባ” የሚሉ ንባብ ቀመስ ወጣቶች አሉ። እኔ የሰማኋቸው አባቶች ግን “ከትናንት ዛሬ ይሻላል” የሚሉ ይመስላል። ሁለት ገጠመኞቼን ላውጋችሁ። (ጨዋታዎቹ በጉራጊኛ ነበሩ። “ቃና ውስጤ ነው” ብለን ወደ አማርኛ መልሰናቸዋል። 🙂 )   ከዚህ ቀደም፥ አንድ ለቅሶ ቤት ውስጥ “የዛሬ ወንዶች ለሚስቶቻቸውና ለልጆቻቸው” እንዲሁም “የድሮ ወንዶች ለሚስቶቻቸውና ለልጆቻቸው” የሚል ርዕስ ጉዳይ ላይ በእድሜ ገፋ ገፋ ያሉ አባቶች ይጫወታሉ። ሁሉም በሚባል ደረጃ፥ የዛሬውን አደነቁ። የእኛ ጊዜ ወንድ “ወተትሽ ገነፈለልሽ። ልጅሽ አለቀሰልሽ።” ነበር የምንለው።… Read more “ትናንት” እና “ዛሬ”

Rate this:

ፍካሬ ንቅሳት

ድሮ ነበር… አንድ በጊዜና በጥረቱ ብዛት ከድህነቱ ተላቅቆ ባለፀጋ የሆነ ሰው ነበረ። ቤቱ ውስጥ በአሽከርነት እንድታገለግለው ከገጠር ያመጡለትን ሴት ገና ሲያያት ይደነግጣል። በወቅቱ ሴቲቱ የለበሰችው አዳፋ ልብስ ነበር። እሱም በዝቶ ገላዋ ላይ ተበጫጭቋል። ለእግሯም ባዶ እግር ከመሆን የማይሻል የተበጣጠሰ ላስቲክ ጫማ (ኮንጎ) ነበራት። ስትራመድ እየጎተተችው፣ ጣቶቿም ወጣ ገባ ይሉ ነበር። እየሮጠች ያስጎነጎነችው የሚመስለው ፀጉሯም ተክበስብሶና አዋራ ተሰግስጎበት ለዓይን አይማርክም። ከጉዞ ብዛት ፊቷን ያወረዛው ላብም ውበቷ ላይ አጥልቶባት ይጨንቃል።   እድሏ ሆኖ ግን በዚህ ሁሉ መሀል የአዲሱ ጌታዋን ልብ ማቅለጥ አልተሳናትም ነበር። ነፍሱ እስክትበር ተከይፎባት ነበር። ባለፀጋው ከሀብቱ ብዛትና ከኑሮው ጥራት… Read more ፍካሬ ንቅሳት

Rate this:

ይሄ ይሄ ሲሰማ ደግሞ…

ጥፋ… ጥፋ…! ሂድ ብረር… ብረር… የሚያሰኙኝ ብዙ ነገሮች አሉ። ልብ ካሉ፥ በየማዕዘኑ የሚሰማው፣ የሚታየው ነገር ለጉድ ነው። “ጆሮ ከመስማት አይሞላም፣ ዐይንም ከማየት አይጠግብም።” መባሉን ስናስብ እንቋቋማለን እንጂ፥ ጉዳችን ነበር። ዛሬ… Read more ይሄ ይሄ ሲሰማ ደግሞ…

Rate this: