Skip to content
Advertisements

Category: ልብ ወለድ

አንዳንዴ…

በሰላሙ ጊዜ የሆድ የሆዳችንን እንጫወት ነበር። ያኔ እኔና አንቺ አፍ አፋፍ፥ ሚስጥር የባቄላ ወፍጮ ነበረ። ሁለታችንም ጋር የሚያድር የለም፤ ጨጓራችን እስኪወቀር፣ ምላሳችን ከረጢቱ እስኪራገፍ ድረስ ተናዘን፥ በወሬ ዱቄት የታጨቀ ከረጢት ከረጢታችንን ሸክፈን እንሄድ ነበር። ነገር ያጋጨን እለት ያቆርሽውን ሁሉ አውጥተሽ ትነቁሪኝ ጀመረ። (ማቆር መቻልሽ የልብ ልብ ሳይሰጥሽም አልቀረ።) መጣላታችን ልብሽ ውስጥ ሲነደፍ አገር በምስጢሬ የወሬ ስንጥቁን፥ ኩታ ሸምኖ አለበሰ። ወዳጅ ያፈራኹበትን ነጻነትና፣ ያኔ ያወራሁት ነጻ ወሬ ሰንኮፍ ሆነው ሰውነቴ ላይ ተሰኩ። ተራማጅነትንም እረፍትንም ነሱኝ። ወዳጁን እንደቀበረ ሰው ቁም ለቁም ጢሜን ነጭቼ አገጬን ተገጠብኩ። ቆጨኝ። ክፉኛ ቆጨኝ። ማውራቴ ቆጨኝ። መስማትሽ ቆጨኝ።… Read more አንዳንዴ…

Rate this:

ባቡር፣ መንገድና የሰው ጠባይ

ተመርቆ የቆየው የባቡር መንገድ ስራ የጀመረ ጊዜ “ከተማችን ዘነጠች” ተባለ። “ዓለሟን አየች” ተባለ። በየልቡ “አሁን ደመቅሽ አዲሳባዬ” ተዘፈነላት። ሰው ደስታውን በተለያየ መንገድ ገለጸ። የትናንት መልካም ታሪኮችን ስለዛሬ መስዋዕት ያቀረቡ አሽቋላጮችም… Read more ባቡር፣ መንገድና የሰው ጠባይ

Rate this:

አንድ አፍታ፡ – ነገረ ቆሎ. . .

ህይወት ቆሎ ናት… ስንዴ ቆሎ ¬ ገብስ ቆሎ -¬ በሽንብራ የተደባለቀች ቆሎ -¬… ጎኗ ሱፍ ቁጭ ቁጭ ብሎ የሚያጅባት ቆሎ…. ሱፍ ለብሰው የሚከኳት ቆሎ… ¬ ሰነፍ ቆሎ፣ ጎበዝ ቆሎ… ¬_ ‘ፓ ቆሎ!’ እያሉ…. እየሰፈሩ የሚቸረችሯት…. የሚቆረጥሟት! የሚቀጯት! እየቆነጠሩ የሚቀጨቅጯት — — ቀጭ ቀምቧ…. ቀምቧ ቀጭ…. ቀጭ ቀምቧ…. …..ቆሎ በአፉ ሞልቶ ቆንጆ ሴት ማለም – ለፈለገ – ቀላል ነው። ወይ ማስቲካዋን፣ ወይ ሂል ጫማዋን አርጋ…. በሊሾው ወለል ላይ፥ ቀጭ ቀንቧ ስትል በሀሳቡ እየሳለ – – – ሂል ቶፕስ – ዳሌዋን ማለም ይችላል። ¬ ‘የ – ኔ – ቆ – ን – ጆ–… Read more አንድ አፍታ፡ – ነገረ ቆሎ. . .

Rate this:

አንድ አፍታ 2

ዙረታም ነች! — የለየላት…!! ኡመቴ ዙረታም! [‘ኡመቴ ምንድን ነው?’ አሃ… በቃ የድሮ የመንደራችን ቃል ነበር። እንደ’ሷ ያለ የሚጠራበት ቃል።] ሰው ኡምት ሲል፣ መላ ቅጡን ሲያጥ ‘ኡመቴ ነው’ ይባላል።…እናም ‘ኡመቴ ናት!’… አገር ምድሩን ስትዞር ነው የምትውለው… ልክ መሬት እንደምትዞር፣ አታርፍም! ዝም ብላ ስትዞር… ዝም ብላ! …… እያወራች ስትዞር… — ሰሚ ፍለጋ! …… እያላወራች ስትዞር….– ወሬ ፍለጋ! …… እየበላች ስትዞር… — ‘እንብላ’ ምትለው ፍለጋ! …… እየራባት ስትዞር….– ምግብ ፍለጋ! …… ሲበሉ ስታይ ስትዞር…–ቅልውጥና! ስታሳዝን! ደግነቱ እንደ’ሷ መዞር አይደለም፤….ከተማው አዙሪት የለውም። — ሲራዳት! ሲረዳት! ሲያረዳት! ሲያርዳት! ለርሷ ቤቷ መመለስ መርዶዋ ነው… … ዞራ… Read more አንድ አፍታ 2

Rate this:

አንድ አፍታ 1

አያት…. አየችው…. አሳቀው… አሳቃት….ተሳሳቁ…. ተሳቀቁ…. አለ አይደል? — እንዲሁ ማስፈገግ! ፈገገገገግ… ተፋገጉ! ፈገገላት…. ፈገገችለት…. ፍግግግግ… !! አሃ! ተፈላለጉ! ዐይን ላይን… ትይትይት…. ፈለጋት….. ፈለገችው…. ፍልግልግ….. ውይ ፍጥነቷ! – እጇ ላይ የወጣውን ፈለግ ከምኔው አሳየችው…. እህ፥ ወይስ አየባት? አዎ አየባት! !! አይቶም አላበቃ ድፍት ብሎ ፈለገገላት! ያው በጥርሱ ፍልግግግ አረገላት… በስታይል እየሳማት! ሳያስቀይስ፣ እንደፈለግ ነቃይ… ሳያስጠጣ… ሳያስጠጣ ከእጇ ላብ ጥጥት! — ጥሙን ቁርጥ! — እርክት! እርክትክት! እርሷም ኩርት! እርክት!… አልደበራትም! አስፈለገገችው! !! ታክሲ ውስጥ ነበሩ! እርሱ ሲወርድ፣ እርሷም ወረደች! ማለት ተያይዘው ወረዱ…. ውርድ፣ ርድ… ርድርድ… ውርድርድ…. ውርድርድርድርድ… ድርድርድርድርድር…. ሸኟቸው! በዜማ ሸኛቸው… “ሲሄዱም… Read more አንድ አፍታ 1

Rate this:

የመጨረሻው ኑዛዜ

በአድናን አሊ e-mail: adnan2000free@yahoo.com አሞራዎቹ ከበውናል። ነብሳችን ሳትወጣ ስጋችንን በጫጭቀው ሊበሉ አሰፍስፈዋል። ጉልበቶቻችን በጠኔ ዝለዋል፤ በረሃብ ደክመናል። ያረፈብንን ዝንብ እንኳ ‘እሽ’ ለማለት እጃችንን ማወናጨፍ አቅቶናል። ደክመናል። መንገዶቻችን ሁሉ ወደ አዘቅት ወስደውናል። አሁንስ የትኛው ተስፋ ቀረን? . . . . . . . . በአሞራዎቹ ከመሰልቀጥ በቀር። እንዲህ ይሆናል ብለን እንዳንናገር አፋችን በሴራ ተተብትቦ ልሳን አልባ ሆነን ኖረናል። ከዝምታችን ብዛት አፋችን ላይ ሸረሪት ድሯን አድርታብናለች። በዚህች እንኳ የሞት ሽረት ትንቅንቅ ውስጥ ልሳናችን ተለጉሟል። “ማን ያውጋ? . . . የነበረ ማን ያርዳ? . . . የቀበረ” . . . ነበር ድሮ። የነበርነውም… Read more የመጨረሻው ኑዛዜ

Rate this: