Skip to content
Advertisements

Day: November 28, 2018

ሴት ነሽና

ሴት ነሽና፥ ሰውነቱን፣ ክብሩን ትቶ፣ ቀሚስሽን ወንድ ይለካል ደግሞ ሲለው ተንጠራርቶ ተጠራርቶ… ደፍሮ ይነካል፤   ሴት ነሽና፥ “ተው” ብትዪው፥ እንደመብቱ “ዝም በይ” ይላል በአንደበቱ፤ ማንም የለም “ተው” የሚለው፣ ሁሉም አጋዥ አበርቺው ነው፤   ሴት ነሽና፥ የሀሳብሽን ቁመት ልቀት የህልምሽን ስፋት ርቀት ወንድ ሰፍሮ ይመዝናል፣ በእርሱ ገበያ ይተምናል፤   ሴት ነሽና፥ በአውሬነቱ እርቃን ቀርቶ፣ ሀፍረት ጥሎ፣ ሱሪ ፈትቶ፣ ሰው ገላ ላይ ይፈነጫል፣ “አሳስታኝ ነው” ብሎ ይጮሃል፤   ሴት ነሽና፥ ለእርሱ ስሜት ለአውሬነቱ ጥጋት ሆኖ ለነውሩ፣ ለሴሰኛ ሟችነቱ አንቺን ያማል ሁሉም ወጥቶ ከየቤቱ፤   ሴት ነሽና፥ እሱ ሰፍሮ አጥሯል ብሎ የደፈረሽን ተንጠላጥሎ፣… Read more ሴት ነሽና

Rate this:

ስለሀሳብ ልዕልና ሲወራ…

ምርጫውን ፍትሀዊ እና ዴሞክራሲያዊ ለማድረግ የተደረገው የቃል ተስፋ መልካም ነው። እግዚግዚአብሔር ፈቅዶ ምርጫው ነጻ ሆኖ ቢከናወን ግን፣ ኢህአዴግ በምን ቁመናው ሊቀጥል ይችላል? 🤔   በርግጥ “ከማያውቁት መልዐክ የሚያውቁት ሰይጣን” በሚል ብሂል የሚገብርላቸው ሊኖር ቢችልም ቅሉ፥ ለክፋታቸው ሲነዙት የኖሩት የብሄር አጀንዳ መልሶ እነሱኑ ሳይሰለቅጥ የሚመለስ በማይመስል መልኩ ተቀጣጥሏልና፥   “ምርጫው በነጻ እና ፍትሀዊ መንገድ እንዲደረግ ፈቃደኞች/ቁርጠኞች ነን” ማለታቸውን በራሱ፣ በሰላም እንደሚለቁ ቃል የገቡ ያህል እቆጥረዋለሁ።   (የሚነደው ግን፥ የነጻ እና ፍትሀዊ ምርጫ ወሬ እና ምኞት እንኳን ካለነሱ ፈቃድ የማይቻል የነበረ መሆኑ ነው። ይኽንንም ውለታ እንደዋሉ እንጂ መሆን እንዳለበት አይቆጥሩትም።)   ኢህአዴግ… Read more ስለሀሳብ ልዕልና ሲወራ…

Rate this: